በ2022 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ሆና ማየት፡፡
በህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የደንብ መተላለፎችንና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከታተልና በመቆጣጠር አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ማራኪና ሰላማዊ እንድትሆን ማድረግ፡፡
አገልግሎቶች
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን
1.3 የደንብ ማስከበር ባለስልጣን (ጽ/ቤት) ስልጣንና ተግባራት
በከተማው አስተዳደር ከደንብ ማስከበር ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦችን፣ ስለሚደረጉ ቁጥጥሮች እና ስለሚወሰዱ ዕርምጃዎች በተለያዩ ዘዴዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ያስጨብጣል፤
የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ በመስራት ደንብ መተላለፍን እንዲቀንስ ያደርጋል፤
ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ማንኛውንም ሕገወጥ ግንባታ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ መሬት መያዝን፣ መሬት መውረርን እና የመሬት ይዞታ ማስፋፋትን ተግባርን ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፣ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
ሕገወጥ የመንገድ ላይ ንግድ፣ የእንስሳትና የስጋ ዝውውር፣ ዕርድ፣ ሽያጭ እና ተያያዥ የሆኑ የደንብ መተላለፍ ተግባራትን ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፣ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
በክፍት እና ዝግ የመናፈሻ ቦታዎች፣ የመንገድ አካፋዬች፣ ዳርቻዎችና አደባባዮች የሚከናወኑ ሕገወጥ ተግባራትን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል እርምጃ ይወስዳል፤
የትራፊክ እንቅስቃሴ እና ደህንነትን የሚያውኩ እና የሚጋርዱ በመንገድ ወይም በትራፊክ መብራት ላይ የሚከናወን ልመናን፣ በመንገድ ላይ የንግድ ዕቃዎችን ለረዥም ጊዜ ማስቀመጥ፣ ዛፍ ወይም አትክልት መትከል፣ ያለፈቃድ ድንኳን መጣል፣ ብየዳ ማድረግ፣ የተበላሸን ተሽከርካሪ ማቆም፣ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ መጠገን ወይም ማስጠገን፣ ማጠብ ወይም ማሳጠብን እንዲሁም ሌላ ማንኛውም የትራፊክ እንቅስቃሴን የሚያውክ ወይም ለአደጋ የሚያጋልጥ ተግባርን ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በቅንጅት ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ ይወስዳል፤
መንገዶችን ማሻሻል፣ መቀየር፣ መቀየስ፣ በበር መዝጋት፣ በኬላ ማጠር መቁረጥን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ ይወስዳል፤
በመንገድ መብራት ምሰሶ፣ በድልድይ፣ በመንገድ ምልክት እና በእግረኛ የመንገድ መከላከያ አጥር ላይ ባነር፣ ማስታወቂያ እንዲሁም በሕገወጥ መንገድ የውጭ ማስታወቂያ መለጠፍ ወይም መትከልን ወይም ማንጠልጠልን ይከላከላል፤ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
በትምህርት ተቋማት ዙሪያ ዕፅ መጠቀሚያ ቤት፣ ፊልም ወይም ቪዲዮ ቤት፣ ጭፈራ ቤት፣ መጠጥ ቤት፣ ቁማር ቤት መክፈትን፣ ጫት ማስቃምን ወይም ሺሻ ማስጨስን በከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
አግባብ ባለው ህግ መሰረት በገንዘብ የሚያስቀጡ የደንብ መተላለፍ ተግባራትን የቅጣት ገቢ ይሰበስባል፣ ህገወጥ ድርጊት የተፈጸመባቸዉን ንብረቶች ይወርሳል፣ በህጋዊ መንገድ ይሸጣል ወይም መወገድ ያለባቸውን ያስወግዳል፤
የፓራ ሚሊተሪ ሠራተኞችን ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ መሰረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤ ያሰናብታል፡፡