ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፦ ህገ-ወጥ የጎዳና እና የበረንዳ ንግድን ለመከላከል የሚያስችል የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ
ግንቦት 11/2018 ዓ.ም
ግንቦት 11/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ — በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት “ህገ-ወጥ የበረንዳ እና የጎዳና ንግድን በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ቃል ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
የአካባቢውን ሰላምና ውበት ለመጠበቅ እንዲሁም የህዝብን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የነዋሪዎች ተወካዮች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የጸጥታ አካላት ተገኝተዋል።
የመድረኩ ዋና ዋና ኩነቶች፦
የመድረኩ መከፈት፦ ዕለቱ በታደሙት የሀይማኖት አባቶች ልዩ ምርቃት እና ጸሎት በይፋ ተጀምሯል።
የሰነድ አቀራረብ፦ በውይይቱ መነሻ የሚሆን ዝርዝር ሰነድ በአቶ አበባው ካሳሁን የቀረበ ሲሆን፣ በሰነዱ ላይም የህገ-ወጥ ንግድ በአካባቢው እንቅስቃሴ፣ በትራፊክ ፍሰት እና በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ እያሳደረ ያለው ተጽዕኖ በሰፊው ተዳሷል።
የህዝብ ተሳትፎ እና ውይይት፦ በመድረኩ ላይ የታደሙት የሰብሰባው ተካፋዮች በተነሳው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ፣ የአካባቢያቸውን ደህንነትና ደንብ ከማስከበር አኳያ ያሉባቸውን ስጋቶችና ጥያቄዎች በነጻነት አንስተዋል።
ማጠቃለያ፦ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱት ዘርፈ-ብዙ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የጽሕፈት ቤቱ የቅድመ መከላከል ሽፍት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ብርሃኔ ሙላቱ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል። ህገ-ወጥ የጎዳና እና የበረንዳ ንግድን ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመከላከል የህብረተሰቡና የደንብ ማስከበር አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን በማስገንዘብ መድረኩ በስኬት ተጠናቋል።
ምንጭ፡- ኮልፌ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት“የደንብ ጥሰት እንዳይፈጸም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው” በሚል መሪ ሐሳብ በአዋጅ ቁጥር 1383/2017 መሰረት የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
መጋቢት 03/2018 ዓ.ም — ኮልፌ ወረዳ 07 ደንብ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው ቀጠና 3 በሚገኘው በሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ 90 ኩንታል የተፈጨ በርበሬ በቁጥጥር ስር ውሎ ከገበያ በፊት ተወግዷል።
በገንዘብ ግምቱ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተው ይህ ምርት በውስጡ ያለው የአፍላቶክሲን መጠን ከፍተኛ መሆኑ በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ ለህብረተሰቡ ጤና አደጋ ሊያመጣ ስለሚችል ከገበያ በፊት እንዲወገድ ተደርጓል።
የምርቱ መገኘት በህብረተሰቡ የተሰጠ ጥቆማ መሰረት ተገንዝቦ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውሏል። በኋላም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተደረገ ምርመራ የአፍላቶክሲን መጠኑ ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጧል።
እርምጃው በአዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት እና ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ተፈፅሟል።
የኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ሙኒራ ነጋሽ እንደገለፁት፣ በምርመራ የአፍላቶክሲን መጠን ከፍተኛ መሆኑ በመረጋገጡ ምርቱ ለህብረተሰቡ ጤና አደጋ እንዳይፈጥር ከገበያ በፊት እንዲወገድ መደረጉን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለጤና አደጋ ሊያመጡ የሚችሉ የምግብና መጠጥ ምርቶችን በአካባቢያቸው ሲያዩ ለተገቢው አካል ጥቆማ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።
ይህ እርምጃ የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ እና የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ኮልፌ ኮሙኒኬሽን
ዜና
ኮልፌ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር – የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 አስተዳደር አስተባባሪነት፣ ለነዋሪዎች ምቹና ጤናማ አካባቢ ለመፍጠር ያለመ “ውብ፣ ፅዱ እና አረንጓዴ ብሎክ” የመፍጠር የፅዳት ንቅናቄ በዛሬው እለት በወረዳው ሁሉም ብሎኮች በድምቀት ተካሄደ።
አስተዳደሩ ለማህበረሰብ ተስማሚ አካባቢ ለማድረግ በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ሲገልጽ፣ የዛሬው የፅዳት ዘመቻም የዚህ ተከታታይ ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።
በንቅናቄው ላይ የወረዳው አመራሮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የየብሎኩ ነዋሪዎች እና በተለይም የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሰራተኞች በብዛት በመሳተፍ የፅዳት ስራውን በተግባር ደግፈዋል። ይህም የህብረተሰብ ንቃትን እና የመንግስት–ህዝብ ትብብርን በግልፅ አሳይቷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መቆያ ላሌ፣ “ፅዱ አካባቢ መፍጠር ለጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ ወሳኝ ነው” በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል። እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ መለየት እንደ ሀብት በመመልከት መጠቀም የፅዳት ስራውን ስኬታማ እንደሚያደርግ ገልጸው፣ “ፅዳት የስልጣኔ መገለጫ ነው” በማለት እያንዳንዱ ዜጋ ለአካባቢው ፅዳትና ውበት ተቆርቋሪ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
ምንጭ፡- ወረዳ 07 ኮምንኬሽንበኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የግንባታ ተረፈ ምርትና ግብዓተ ምርቶችን በኮሪደር መሠረተ-ልማት ላይ በማስቀመጥ ልማቱን ያበላሸ ድርጅት 100 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ፡፡
26/05/2018 ዓ.ም
*ቤተል*
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ልዩ ቦታው ቀጠና 06 መንዲዳ መውጫ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቀን 26/05/2018 ዓ.ም በኮሪደር መሰረተ-ልማቱ ላይ የግንባታ ተረፈ ምርትና ግብዓተ ምርቶችን በማሰቀመጥ ልማቱን ያበላሸው ሶከም ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት ላይ እርምጃ በመውሰድ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱን አስታወቀ።
የወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የጋራ ሀብት የሆነውን የኮርደር ልማትእና በሌሎች ቀጠናዎች የሚገኙ መሠረተ ልማቶችን ጉዳት በሚያደርሱት እና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሥምሪት አሰጣጡን በማጠናከር ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ሥራችንን በመቀጠል ሀላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
መረጃው :- የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
የህዝብና የመንግስት ሀብት የሆነውን መሬት ከህገ-ወጥ ወረራ በመከላከልና በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ውጤት የመጣ መሆኑን ተገለጸ።
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
ኮልፌ ወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን
የኮልፌ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት የሕዝብና የመንግስት ሀብት የሆነዉ መሬት ለታለመለት አላማ ብቻ እንድዉልና መሬት ወረራ መከላከል መቻሉን የፅ/ቤት ሃላፊዉ አቶ ቦጃ ከበደ ገልፀዉ በተለይም ባንክ የገቡ 632 መሬቶች በወረዳዉ መኖራቸዉንና ለታለመላቸዉ አላማ ብቻ እየዋሉ እና እና በሕገ ወጦች እንዳይወሩ በልዩ ትኩረት እየጠበቀ መሆኑን አስታውቀዉ በአጠቃላይ በወረዳችን በቁጥር 928,252 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውና በመሬት ባንክ ውስጥ የሚገኝ የመንግስት መሬት በአግባቡ ተለይቶ ጥበቃ እየተደረገለት ይገኛል።
እነዚህ ቦታዎች ለመንግስት ለልማት ስራዎች እስኪውሉ ድረስ በህገ-ወጥ ወራሪዎች እንዳይያዙ የመለየትና የታፔላ የማቆም ስራ መከናወኑና የደንብ መተላለፎችን በዘላቂነት ለመከላከል ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገለጸው ጽህፈት ቤቱ፣ ከነዋሪዎችና ባለ ድርሻ አካላት ጋር ያላቸውን ትብብር በማጠናከር መሬት ወረራን እንዲሁም ሌሎች ደንብ መተላለፎችን መከላከላቸዉን
የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በቀጣይም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡
በመጨረሻም በወረዳው ውስጥ እየተሰሩ የሚገኙ የልማትት ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም በመሆን የሀገር ኢኮኖሚ እድገት፣ ማህበራዊ አንድነት በማረጋገጥ ሰላም ፀጥታ በማስጠበቅና ደህንነት በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የበጎ ተግባር ተሳትፎ ማድረጉን ተገለጸ፡፡!!!
ኮልፌ ወረዳ 07 ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 21/2018ዓም
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት የወረዳው ኦፊሰሮች በማስተባበር ከሽፍታቸው ዉጭ የሆኑትን የእረፍት ሰዓታቸዉን በመጠቀም በወረዳዉ ዙሪያ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ምርታቸው በዝናብ እንዳይበላሽ በአጨዳ በማገዝና የማበረታታት ስራ መሰራቱን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቦጃ ከበደ ገልፀዋል ።
አክለውም ከበጎ - ፈቃድ አገልግሎት አንዱ የሆነዉ አርሶ አደሮችን በአጨዳ የማገዝ ተግባር ሲሆን እንደ ወረዳ እና እንደ ክፍለ ከተማችን በተያዘዉ በጀት በርካታ ሰው ተኮር እና በጎ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል።
#ደም_በመለገስ_የእናቶችና_ህጻናት_ሕይወት_እንታደግ!” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ ንቅናቄ ተካሄደ
#ኮልፌ_ወረዳ_07_ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 07 ደንብ አስተዳደር ጽ/ቤት አስተባባሪነት አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ በጎ ፈቃደኞች
በደም እጥረት ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፍ እናቶችንና ህጻናትን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ “ደም በመለገስ የእናቶችና ህጻናት ሕይወት እንታደግ!” የደም ልገሳ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
ንቅናቄው በተለይ በወሊድ ወቅት እና በድንገተኛ አደጋ የሚያጋጥሙ ችግሮች ለሚከሰት ከፍተኛ የደም መፍሰስን ለመከላከልና በደም ማነስ ለሚጠቁ ህጻናት ተገቢውን ህክምና ለመስጠት የሚያስችል በቂ ደም እንዲኖር ያለመ መሆኑን ተገልጿል።
Abiy Ahmed Ali (Oromo: Abiyi Ahmed Alii; Amharic: ዐቢይ አሕመድ ዐሊ; born 15 August 1976) is an Ethiopian politician serving as the third Prime Minister of Ethiopia since 2018, and as the leader of the Prosperity Party since 2019.[1][2] He was awarded the 2019 Nobel Peace Prize “for his efforts to achieve peace and international cooperation, and in particular for his decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea“..
The president of Ethiopia is the head of state of Ethiopia. The position is largely ceremonial with executive power vested in the Council of Ministers chaired by the prime minister. The current president Taye Atske Selassie Amde (Amharic: ታዬ አጽቀሥላሴ, born 13 January 1956) is an Ethiopian diplomat and politician who is serving as president of Ethiopia since 7 October 2024. He has worked as ambassador on numerous occasions in the United Nations. Prior to assuming this role, he served as the Minister of Foreign Affairs.
Adanech Abebe (Oromo: Adaanach Abeebee) is an Ethiopian politician and attorney who is serving as the thirty-second mayor of Addis Ababa since 2021. She has been serving as a deputy mayor from 2020 until 2021. She previously was the Minister of Revenue and Customs Authority from 2018[1][2] to 2020, when she became the first female to assume the role of the Federal Attorney General of Ethiopia.[3][4][5][6] She is the first woman to hold the mayorship since it was created in 1910.[